am_tn/rom/03/03.md

2.2 KiB

አንዳንድ አይሁዶች እምነት ባይኖራቸውስ? አለማመናቸው የእግዚአብሔርን ታማኝነት ያስቀራልን?

ጳውሎስ ሰዎች እንዲያስቡ እነዚህን ጥያቄዎች ይጠቀማል። “አንዳንድ አይሁዶች ለእግዚአብሔር ታማኝ አልነበሩም። ከዚህ በመነሣት እግዚአብሔር የገባውን ቃል ኪዳን መፈጸም አይችልም ብለን መደምደም አለብንን?”

በጭራሽ አይሆንም

ይህ እንደማይሆን ይህ አገላለጽ አጥብቆ ይቃወማል፡፡ እዚህ ላይ ልትጠቀምበት የምትችለው በቋንቋህ ተመሳሳይ አገላለጽ ሊኖርህ ይችላል፡፡ “ፈጽሞ ሊሆን አይችልም!” ወይም “በጭራሽ አይሆንም!”

ይልቁንስ

“ይልቁንስ ማለት አለብን”

ይልቁንስ እግዚአብሔር እውነተኛ ይሁን

እግዚአብሔር ሁል ጊዜ እውነተኛ ነው እናም ቃል ኪዳኑን ይጠብቃል፡፡ “እግዚአብሔር ሁል ጊዜ የገባውን ቃል ኪዳን ይፈጽማል”

እያንዳንዱ ሰው ውሸተኛ ቢሆን

“እያንዳንዱ” እና “ውሸተኛ” የሚሉት ቃላት እግዚአብሔር ለቃል ኪዳኑ ሁልጊዜ እውነተኛ መሆኑን አፅንኦት ለመስጠት የተጋነኑ ቃላት ናቸው፡፡ “ምንም እንኳ እያንዳንዱ ሰው ሐሰተኛ ቢሆን”

እንደ ተጻፈው

ይህንን በአድራጊ ቅርፅ ልትተረጉመው ትችላለህ። “ቅዱሳት መጻሕፍት ራሳቸው እኔ ከምናገረው ጋር ይስማማሉ”

በቃልህ ጻድቅ መስለህ ልትታይ ትችል ይሆናል፣ ወደ ፍርድም በመጣህ ጊዜ የምትረታ ሊመስልህ ይችላል

እነዚህ ሁለት ሐረጎች በጣም ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ ይህንን በአድራጊ ቅርፅ ልትተረጉመው ትችላለህ። “እያንዳንዱ ሰው የምትናገረው ነገር እውነት መሆኑን መቀበል አለበት፣ እናም ማንም ሰው ቢቃወምህ ሁል ጊዜ በጉዳይህ ላይ ታሸንፋለህ”