am_tn/rom/03/01.md

2.0 KiB

አያያዥ መግለጫ

እግዚአብሔር ሕጉን ስለ ሰጣቸው አይሁዶች ተጠቃሚዎች መሆናቸውን ጳውሎስ ያውጃል፡፡

እንግዲህ የአይሁዳዊ ብልጫው ምንድን ነው? የመገረዝ ጥቅሙ ምንድን ነው?

ጳውሎስ በምዕራፍ 2 ላይ የጻፈውን ከሰሙ በኋላ ሰዎች ሊኖራቸው የሚችሏቸውን ሀሳቦች ያቀርባል። ይህንን ያደረገው በቁጥር 2 ላይ ለእነርሱ መልስ ለመስጠት ነው። “አንዳንድ ሰዎች ‘ታዲያ አይሁዳዊው ምን ጥቅም አለው? እና የመገረዝ ጥቅሙስ ምንድን ነው?ይሉ ይሆናል'” ወይም “አንዳንድ ሰዎች ምናልባት ደግሞ ‘ያ እውነት ከሆነ አይሁዶች ምንም ጥቅም የላቸውም፣ እንዲሁም መገረዝም ምንም ፋይዳ የለውም ይሉ ይሆናል፡፡'”

በየትኛውም መንገድ ጥቅሙ ብዙ ነው

ጳውሎስ አሁን በቁጥር 1 ላይ ለተነሡት አሳቦች ምላሽ ይሰጣል። እዚህ ላይ “ይህ” የሚያመለክተው የአይሁድ ሕዝቦች አባል መሆንን ነው፡፡ “ግን አይሁዳዊ መሆን ትልቅ ጥቅም አለው”

በመጀመሪያ

ተቀባይነት ያላቸው ትርጉሞች 1) “በመጀመሪያ በጊዜ ቅደም ተከተል” ወይም 2) “በጣም በእርግጠኝነት” ወይም 3) “እጅግ በጣም በአስፈላጊነት” ናቸው፡፡

አይሁዶች ከእግዚአብሔር መገለጥ በአደራ ተሰጥቷቸዋል

እዚህ ላይ “መገለጥ” የሚለው ቃል የእግዚአብሔርን ቃሎች እና ቃል ኪዳኖችን ያሳያል፡፡ ይህንን በአድራጊ ቅርፅ ልትተረጉመው ትችላለህ። “እግዚአብሔር ቃል ኪዳኖቹን የያዘውን ቃሎቹን ለአይሁድ ሰጥቷል”