am_tn/rom/02/21.md

1.9 KiB

አንተ ሌሎችን የምታስተምር ራስህን አታስተምርምን?

ጳውሎስ አድማጮቹን ለመገሰጽ ጥያቄን ይጠቀማል። ይህንን እንደ ጠንካራ መግለጫ ልትተረጉመው ትችላለህ፡፡ “ሌሎችን ታስተምራለህ ግን ራስህን አታስተምርም!” ወይም “ሌሎችን ታስተምራለህ፣ ግን የምታስተምረውን አታደርግም!”

አትስረቅ ብለህ የምትሰብክ ትሰርቃለህን?

ጳውሎስ አድማጮቹን ለመገሰጽ ጥያቄን ይጠቀማል። ይህንን እንደ ጠንካራ መግለጫ ልትተረጉመው ትችላለህ፡፡ AT: “ሰዎች እንዳይሰርቁ ትነግራለህ፣ አንተ ግን ትሰርቃለህ!”

ማንም ማመንዘር የለበትም ብለህ የምትናገር ታመነዝራለህን?

ጳውሎስ አድማጮቹን ለመገሰጽ ጥያቄን ይጠቀማል። ይህንን እንደ ጠንካራ መግለጫ ልትተረጉመው ትችላለህ፡፡ “ሰዎችን እንዳያመነዝሩ ትነግራለህ፣ አንተ ግን ታመነዝራለህ!”

ጣኦትን የምትጠላ፣ ቤተ መቅደሶችን ትዘርፋለህን?

ጳውሎስ አድማጮቹን ለመገሰጽ ጥያቄን ይጠቀማል። ይህንን እንደ ጠንካራ መግለጫ ልትተረጉመው ትችላለህ፡፡ “ጣኦትን እንደምትጠላ ትናገራለህ፣ ነገር ግን ቤተ መቅደሶችን ትዘርፋለህ!”

ቤተ መቅደሶችን መዝረፍ

ተቀባይነት ያላቸው ትርጉሞች 1) “ከአሕዛብ የአጥቢያ ቤተ መዝቅደሶች ቁሳቁሶችን መስረቅ እና ትርፍ ለማግኘት መሸጥ” ወይም 2) “ለእግዚአብሔር የሆነውን ገንዘብ ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ አለመላክ”፡፡