am_tn/rom/02/13.md

1.7 KiB

አያያዥ መግለጫ

ጳውሎስ ለእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም መታዘዝ፣ ሕጉ የሌላቸውም ሰዎች ብቻ ሳይሆን ሕጉ ያላቸውንም እንደሚጨምር አንባቢው እንዲያውቅ መግለጹን ቀጠለ፡፡

ቁጥር 14 እና 15 ጳውሎስ ለአንባቢው የሚሰጠውን ተጨማሪ መረጃ ያቋርጣሉ፡፡ እንደዚህ ዓይነቱን ማቋረጥ በቋንቋህ ምልክት የምታደርግበት መንገድ ካለህ፣ እዚህ ላይ መጠቀም ትችላለህ፡፡

የሕጉ አዳማጮች አይደሉም

እዚህ ላይ “ሕጉ” የሙሴን ሕግ ያመለክታል። “የሙሴን ሕግ የሚሰሙ ብቻ አይደሉም”

በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን የሆኑ ማን ናቸው

“እግዚአብሔር እንደ ጻድቃን የሚቆጥራቸው”

ነገር ግን ሕግን የሚያደርጉ

“ነገር ግን እነርሱ የሙሴን ሕግ የሚታዘዙ ናቸው”

የሚጸድቀው ማን ነው?

ይህንን በአድራጊ ቅርፅ መተርጎም ትችላለህ። “እግዚአብሔር የሚቀበለው እርሱ”

ሕግ የሌላቸው አሕዛብ . . . ለራሳቸው ሕግ ናቸው

“ለራሳቸው ሕግ” የሚለው ሐረግ ማለት እነዚህ ሰዎች በተፈጥሮአቸው የእግዚአብሔርን ሕጎች ይታዘዛሉ ማለት ነው፡፡ “የእግዚአብሔር ሕጎች ቀድሞውኑ በውስጣቸው ነበራቸው”

ሕጉ የላቸውም

እዚህ ላይ “ሕጉ” የሙሴን ሕግ ያመለክታል። “በመሠረቱ እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጣቸው ሕጎች የላቸውም”