am_tn/rom/02/08.md

2.3 KiB

አያያዥ መግለጫ

ይህ ክፍል ምንም እንኳን ሃይማኖተኛ ስላልሆነ ኃጢአተኛ ሰው የሚናገር ቢሆንም፣ ጳውሎስ አይሁድ ያልሆኑትም ሆኑ አይሁዶች በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአተኞች መሆናቸውን በመግለጽ ጠቅለል አድርጎ ገልጾታል፡፡

በራስ መፈለግ

“ራስ ወዳድ” ወይም “ራሳቸው ስለሚደሰቱበት ብቻ ግድ የሚላቸው”

እውነትን የማይታዘዙ ነገር ግን ጽድቅ ያልሆነውን የሚታዘዙ

እነዚህ ሁለት ሐረጎች በመሠረቱ አንድ ዓይነት ናቸው፡፡ ሁለተኛው የመጀመሪያውን ያጠናክራል።

ቁጣ እና የመረረ ንዴት ይመጣል

“ቁጣ” እና “የመረረ ንዴት” የሚሉት ቃላት በመሠረቱ አንድ ዓይነት ናቸው፤ የእግዚአብሔርን ቁጣ አፅንኦት ይሰጣሉ፡፡ “እግዚአብሔር እጅግ መቆጣቱን ያሳያል”

ቁጣ

እዚህ ላይ “ቁጣ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው እግዚአብሔር በኃጢአተኛ ሰዎች ላይ የሚመጣውን ከባድ ቅጣት የሚገልጽ ነው።

መከራና ጭንቀት

“መከራ” እና “ጭንቀት” የሚሉት ቃላት በመሠረቱ አንድ አይነት ትርጉም ያላቸው ሲሆን፣ እዚህ ላይ አፅንኦት የሚሰጡት የእግዚአብሔር ቅጣት ምን ያህል መጥፎ እንደሆነ ነው፡፡ “አሰቃቂ ቅጣት ይሆናል”)

በእያንዳንዱ የሰው ነፍስ ላይ

እዚህ ላይ፣ ጳውሎስ “ነፍስ” የሚለውን ቃል መላውን ሰው ለማመልከት እንደ መነጋገሪያ ዘዴ ይጠቀማል፡፡ “በእያንዳንዱ ሰው ላይ”

ክፉ ነገሮችን የተለማመደ

“ሁልጊዜም መጥፎ ነገሮችን የሚሠራ”

አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው

“እግዚአብሔር አስቀድሞ በአይሁድ ሕዝብ ላይ፣ ከዚያም አይሁድ ባልሆኑት ሕዝቦች ላይ ይፈርዳል”

አስቀድሞ

ተቀባይነት ያላቸው ትርጉሞች 1) “መጀመሪያ ከጊዜ አንጻር” ወይም 2) “በእርግጠኝነት”