am_tn/rom/02/05.md

1.9 KiB

አያያዥ መግለጫ

ጳውሎስ ሕዝቡ ሁሉ ኃጢአተኛ መሆኑን ሕዝቡን ማስታወሱን ቀጥሎአል፡፡

ነገር ግን በደንዳናውና ንስሐ የማይገባው ልብህ ልክ

ጳውሎስ እግዚአብሔርን ለመታዘዝ የማይፈልገውን ሰው ለመግለጽ ልቡን ከጠንካራ ድንጋይ ጋር በማነጻጸር ገልጾታል፡፡ እንዲሁም የግለሰቡን አእምሮ ወይም ውስጣዊ ማንነት ለመግለጽ “ልብ” የሚለውን ዘይቤ ይጠቀማል። “ለማዳመጥና ንስሐ ለመግባት አሻፈረኝ በማለቱ ምክንያት ነው”

ደንዳና እና ንስሐ የማይገባ ልብ

ይህን “ንስሐ የማይገባ ልብ” በማለት ማጣመር ይቻላል።

በራስህ ላይ ቁጣን አከማችተሃል

“ማከማቸት” የሚለው ሐረግ የሚያመለክተው ብዙውን ጊዜ ሀብቱን የሚሰበስብ እና በአስተማማኝ ቦታ የሚያኖርን ሰው ነው፡፡ ጳውሎስ በሀብት ፋንታ ግለሰቡ የእግዚአብሔርን ቅጣት እየሰበሰበ ነው ብሏል፡፡ ንስሐ ሳይገቡ በቆዩበት መጠን ቅጣታቸውም ከባድ ይሆናል፡፡ “ቅጣታችሁን የከፋ ታደርጋላችሁ”

በቁጣ ቀን . . . የእግዚአብሔር የጽድቅ ፍርድ የሚገለጥበት ቀን

እነዚህ ሁለቱም ሐረጎች የሚያመለክቱት ያንኑ ቀን ነው፡፡ “እግዚአብሔር ቁጣውን ለሁሉም ሲያሳይ፣ ለሰው ሁሉ በትክክል ይፈርዳል”

ይከፍላል

“ትክክለኛ ዋጋ ወይም ቅጣት ይሰጣል”

ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ሥራው

“እያንዳንዱ ሰው በሠራው ሥራ መጠን”

ፈለጉ

x