am_tn/rom/02/03.md

2.4 KiB

ነገር ግን ይህን አስብ

‹‹ስለዚህ ይህንን አስብ›› ወይም ‹‹ስለሆነም፣ ይህንን አስብ››

ይህን አስብ

‹‹እኔ ልነግርህ ያለሁትን አስብ››

ግለሰብ

ለሰው ዘሮች ሁሉ የምትጠቀምበት አጠቃላይ ቃል ነው ‹‹አንተ ማንም ብትሆን›

እነዚህን በሚያደርጉት ላይ የምትፈርድ አንተው ራስህ ያንኑ ነገር ታደርጋለህ

‹‹አንድን ሰው የእግዚአብሔር ቅጣት ይገባዋል ብለህ የምትፈርድ አንተው ያንኑ ክፉ ነገር ታደርጋለህ››

ከእግዚአብሔር ፍርድ ታመልጣለህን?

ይህ ማስገንዘቢያ በጥያቄ መልክ የቀረበው አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ ይህንን ጥያቄ እንደ አንድ ጠንካራ አሉታዊ መግለጫ አድርገህ ልትተረጉመው ትችላለህ፡፡ ‹‹አንተ በእርግጥ የእግዚአብሔርን ፍርድ አታመልጥም››

የእርሱን መልካም ባለጠግነት፣ ቅጣቱን ማዘግየቱን፣ እና ታጋሽነቱን … ወደ ንስሐ እንደሚመራህ ሳታውቅ ትንቃለህን?

ይህ ማስገንዘቢያ ትኩረት እንዲያገኝ በጥያቄ መልክ ቀርቦአል፡፡ ይህንን እንደ ጠንካራ መግለጫ አድርገህ መተርጎም ትችላለህ፡፡ ‹‹እግዚአብሔር መልካም ስለሆነ ሰዎችን ለብዙ ጊዜ ይታገሳቸዋል ስለዚህ ይህ መልካመነቱ ንስሓ እንዲገቡ ያደርጋቸዋልና ምንም አይደለም የሚል ሁኔታ ሊኖርህ አይገባም››

የትእግስቱን---ባለጠግነት ትንሽ እንደሆነ ታስባለህ

‹‹ባለጠግነቱንና --- ትእግስቱን እንደማያስፈልግ›› ወይም ‹‹መልካም እንዳልሆነ --- ትቆጥራለህ››

የእርሱ መልካምነት ወደ ንስሓ የሚመራህ መሆኑን አታውቅምን?

ይህ ማስገንዘቢያ ትኩረት እንዲያገኝ በጥያቄ መልክ ቀርቦአል፡፡ ይህንን እንደ ጠንካራ መግለጫ አድርገህ መተርጎም ትችላለህ፡፡ ‹‹እግዚአብሔር መልካም እንደሆነ የሚያሳይህ አንተ ንስሓ እንድትገባ እንደሆነ ማወቅ አለብሕ››