am_tn/rom/02/01.md

2.6 KiB

አያያዥ መግለጫዎች

ጳውሎስ ሰዎች ሁሉ ኃጢአተኞች እንደሆኑና ክፉዎች ስለመሆናቸው ማሳሰቡን ያረጋግጣል፡፡

ስለዚህ የምታመካኝበት የለህም

‹‹ስለዚህ›› የሚለው ቃል የጽሑፉ አዲስ መስመር መጀመሪያ ነው፡፡ እንዲሁም ጳውሎስ በሮሜ 1፡1-32 ለተናገረው መደምደሚያ ይሆናል። “እግዚአብሔር ኃጢአትን በተደጋጋሚ የሚያደርጉትን የሚቀጣ ከሆነ፣ በእርግጥ ለኃጢአታችሁ ይቅርታ አያደርግም።”

አንተ ነህ

ጳውሎስ እዚህ ላይ ሲጽፍ ልክ ከእርሱ ጋር ለሚከራከር አንድ አይሁዳዊ እንደሚጽፍ አድርጎ ነው፡፡ ጳውሎስ ይህን የሚያደርገው እግዚአብሔር ኃጢአትን በማድረግ የሚጸኑትን እንደሚቀጣ የሚጽፍላቸውን አይሁዶች ቢሆኑ አሕዛብ+ ለማስገንዘብ ነው፡፡

አንተ

ይህ ‹‹አንተ›› የሚለው ተውላጠ ስም የተናጠል ስም ነው፡፡

ራስህ አንተ፣ ፈራጅ የሆንከው

ጳውሎስ ‹‹አንተ›› የሚለውን ቃል የሚጠቀመው ማንኛውም ራሱን እንደ አምላክ የሚቆጥርና በሌሎች ላይ የሚፈርደውን ለመገሰጽ ነው፡፡ ‹‹አንተ ራስህ ሰብኤ ፍጥረት ሆነህ እያለ የእግዚአብሔር ቅጣት ይገባቸዋል በማለት በሌሎች ላይ ትፈርዳለህ››

በሌላው ላይ በምትፈርድበት ነገር ሁሉ ራስህን ትኮንናለህ

‹‹እነርሱ እንደሚያደርጉት አንተም ታደርጋለህና በራስህ ላይ ትፈርዳለህ››

ነገር ግን እኛ እናውቃለን

እዚህ ላይ ‹‹እኛ›› የሚለው ተውላጠ ስም ክርስቲያን አማኞችንና ክርስቲያን ያልሆኑ አይሁዶችን የሚያጠቃልል ነው፡፡

እንደዚህ በሚያደርጉትም ላይ የእግዚአብሔር ፍርድ ትክክለኛ መሆኑን እናውቃለን

እዚህ ላይ ጳውሎስ ስለ ‹‹እግዚአብሔር ፍርድ›› ሲናገር ሕያው እንደሆነ በሰዎች ላይ ‹‹ሊወድቅ›› እንደሚችል አድርጎ ነው፡፡ ‹‹እግዚአብሔር እነዚያን ሰዎች በእውነትና በተገቢው ሁኔታ ይፈርድባቸዋል››

እነዚያን ነገሮች የሚለማመዱ

‹‹እነዚያን ክፉ ነገሮች የሚያደርጉ ሰዎች››