am_tn/psa/144/009.md

1.8 KiB

አዲስ ቅኔ

ሊሆን የሚችለው ትርጉም 1) ከዚህ ቀደም ተቀኝተኸው ማታቀውን ቅኔ 2) ከዚህ ቀደም ማንም ተቀኝቶት ማያውቀውን ቅኔ

የሚሰጥ…ለነገስታት መድሃኒት

“አንተ የምትሰጥ” …ለነገስታት አንተ መድሃኒት የምትሰጥ

ባሪያውን ዳዊትን

ዳዊት እራሱን እንደ ሌላ ሰው አድርጎ ይናገራል፡፡ “እኔ ዳዊት ያንተ ባሪያ”

ከክፉ ሰይፍ

ዳዊት ክፉ ሰዎችን እንደ ሰይፍ መሳሪያ መስሎ ይናገራል፡፡ “እኔን ለመግደል ከሚፈልጉ ከክፉ ሰዎች”

አድነኝ

እባክህ አድነኝ ነፃ አውጣኝ

ከባእድ ልጆች እጅ

“እጅ” የሚለው ቃል ሃይልን ያመለክታል፡፡ በመዝሙረ ዳዊት 144፡7-8 ላይ እንዴት እንደ ተረጎመው ተመልከት፡፡ “ከባዕድ ልጆች ሃይል”

አፋቸው ምናምንን ከሚናገር

“አፋቸው” የሚለው ቃል የሚናገረውን ሰው ያመለክታል፡፡ በመዝሙረ ዳዊት 144፡7-8 ላይ እንዴት እንደ ተረጎመው ተመልከት፡፡ “ምናምንን ይናገራሉ”

እየማሉ እንኳን ይክዳሉ

ሊሆን የሚችለው ትርጉም 1) ዳዊት የሚናገረው በፍርድቤት ቀኝ እጃቸውን አንስተው የሚምሉ ከሆነ የሚናገሩት ነገር ሁሉ እውነት መሆን አለበት፡፡ “ምለው እንኳን እውነት አይናገሩም ይክዳሉ” 2) ቀኝ እጅ የሚያመለክተው ሀይል እና ጉልበትን ሲሆን “የሚያገኙት ነገር ሁሉ በውሸት ነው፡፡” መዝሙረ ዳዊት 144፡7-8 እንዴት እንደ ተረጎመው ተመልከት፡፡