am_tn/psa/140/001.md

1.1 KiB

አጠቃላይ ሃሳብ

ተመሳሳይነት በዕብራውያን ስነግጥም የተለመደ ነው

ለመዘምራን አለቃ

ይህ ቃል ለዝማሬ/አምልኮ መሪ የተጠቀመው ነው

የዳዊት መዝሙር

ሊሆን የሚችለው ትርጉም 1) ዳዊት መዝሙሩን ነው የፃፈው 2) መዝሙሩ ስለ ዳዊት ነው የሚናገረው 3) መዝሙሩ የዳዊት መዝሙር አይነት ነው፡፡

ለሰልፍ ያከማቻሉ

“ለሰልፍ” የሚለው ጦርነት እና ግጭቶችን ያመለክታል

ምላሳቸው እንደ እባብ

ግጭትን የሚፈጥሩ ሰዎችን ልክ እንደ እባብ ምላስ መስሎ ይናገራል፡፡ እባብ በምላሱ ምንም አይነት ጉዳት አያደርስም ነገር ግን ሲናደፍ እና በውስጡ ያለው መርዝ ነው፡፡ ሰውም ምላሱ እንደ እባብ ነው ሳይሆን የሚያስረዳው ችግርን ከመፍጠር አንፃር ስለሆነ ሲሆን አንዳንድ እባቦች በምላሳቸው መርዝ ስላላቸውም ነው፡፡