am_tn/psa/128/001.md

1.4 KiB
Raw Permalink Blame History

አጠቃላይ ሃሳብ

ተመሳሳይነት በዕብራውያን ስነግጥም የተለመደ ነው

መዝሙረ መዐርግ

ሊሆን የሚችለው ትርጉም 1) “ለማክበር ሕዝቡ ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄዱ የዘመሩት መዝሙር ነው፡፡” ወይም 2) “ወደ መቅደሱ ለመግባት ሕዝቡ የዘመሩት መዝሙር ነው” ወይም 3) “ቃላቶቹ እንደ እርምጃ የሆኑ መዝሙሮች ናቸው”፡፡ በመዝሙረ ዳዊት 120፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎመው ተመልከት

እግዚአብሔርን የሚፈሩት ሁሉ፣ በመንገዶቹም የሚሄዱ ምስጉኖች ናቸው።

ይህ ሐረግ እግዚአብሔር የሚፈሩትን እና የሚያከብሩትን ሁሉ እንደሚባርክ ይናገራል፡፡ “እግዚአብሔር የሚፈርቱን ሁሉ ይባርካል፡፡”

የድካምህን ፍሬ

የሰው ልጅ ሥራን ሰርቶ፣ ደክሞ ፍሬውን ያገኛል፣ የሥራህን ውጤት

መልካምም ይሆንልሃል፡፡

መልካምም የሚለው ቃል የእግዚእብሄርን ፈቃድ እና ፍላጎት ያሳያል፡፡ “እግዚአብሔር ይባርክሃል ደግሞም መልካም ይሆንልሃል፡፡” ወይም “እግዚአብሔር መልካም ያደርግልሃል በረከትንም ያደርግልሃል፡፡”