am_tn/psa/120/001.md

1.0 KiB

አጠቃላይ ሃሳብ

ተመሳሳይነት በዕብራውያን ስነግጥም የተለመደ ነው

መዝሙረ መዐርግ

ሊሆን የሚችለው ትርጉም 1) “ለማክበር ሕዝቡ ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄዱ የዘመሩት መዝሙር ነው፡፡” ወይም 2) “ወደ መቅደሱ ለመግባት ሕዝቡ የዘመሩት መዝሙር ነው” ወይም 3) “ቃላቶቹ እንደ እርምጃ የሆኑ መዝሙሮች ናቸው”፡፡

በተጨነኩ ጊዜ

“በተቸገርኩ ጊዜ” ወይም “ተቸግሬ በነበረበት ጊዜ”

ነፍሴን አድናት

“ነፍሴን” የሚለው ቃል ሙሉ ሰውን ያመለክታል፡፡ “አድነኝ”

ከዓመፀኛ ከንፈር ከሸንጋይም አንደበት

“ከንፈር” እና “አንደበት” የሚሉት ቃላት ውሸት የሚናገሩ እና ሸንጋይ ሰዎችን ያመለክታል፡፡ “እኔ ላይ ከሚያምፁ እና እኔን ከሚሸነግሉኝ ሰዎች”