am_tn/psa/118/026.md

1.1 KiB

በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረከ ነው

እዚህ ላይ ካህናቱ ለንጉሡ መናገር ይጀምራሉ።

በእግዚአብሔር ስም የሚመጣው

እዚህ ላይ “ስም” የሚለው ቃል የእግዚአብሔርን ኃይል የሚወክል ነው፡፡ “በእግዚአብሔር ኃይል የሚመጣው”

እኛ ከእግዚአብሔር ቤት ባረክናችሁ

እዚህ ላይ ካህናቱ ለሕዝቡ ይናገራሉ፡፡

የእግዚአብሔር ቤት

“ቤት” የሚለው ቃል ቤተ መቅደሱን ያመለክታል፡፡ “የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ”

እርሱ ብርሃን ሰጥቶናል

ጸሐፊው እግዚአብሔር ሕዝቡን ስለ መባረኩ ሲናገር ልክ እግዚአብሔር ብርሃንን በላያቸው እንዳበራ አድርጎ ነው፡፡ “ባርኮናል”

መሥዋዕቱን በገመድ እሰሩ

“መሥዋዕቱን በገመድ እሰሩ”

አንተ አምላኬ ነህ

እዚህ ላይ ጸሐፊው እግዚአብሔርን በቀጥታ መናገር ይጀምራል፡፡