am_tn/psa/118/015.md

921 B

የእልልታና የደስታ ድምፅ በጻድቃን ድንኳን ተሰማ

ይህ በአድራጊ ቅርፅ ሊገለፅ ይችላል፡፡ “ሰዎች የደስታና የድል ድምፅ በጻድቃን ድንኳኖች ውስጥ ሰሙ” ወይም “ጻድቃን በድንኳኖቻቸው ውስጥ ስላገኙት ድል እልል አሉ”

የእግዚአብሔር ቀኝ እጅ ድል አደረገች

እዚህ ላይ “እጅ” የሚለው ቃል የእግዚአብሔርን ኃይል ይወክላል፡፡ “እግዚአብሔር በታላቅ ኃይሉ አሸነፈ”

የእግዚአብሔር ቀኝ እጁ ከበረ

እዚህ ላይ፣ እጅን ማንሣት የድል ምልክት ነው። ይህ በአድራጊ ቅርፅ ሊገለፅ ይችላል፡፡ “እግዚአብሔር ቀኝ እጁን አከበረ” ወይም “እግዚአብሔር ቀኝ እጁን በድል አነሣ”