am_tn/psa/118/005.md

1.4 KiB

ነጻ አድርገኝ

ጸሐፊው ስለ እግዚአብሔር የሚናገረው ከአንድ ጠባብ እስር ቤት አውጥቶ በነፃነት መንቀሳቀስ ወደሚችልበት ሰፊ ስፍራ እንደ ወሰደው ልክ እንደዚሁ ከጭንቀት እንዳዳነው ነው፡፡

ሰው ምን ያደርገኛል?

ጸሐፊው ይህንን የአጻጻፍ ጥያቄ የሚጠይቀው እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለሆነ ማንም ሰው ሊጎዳው እንደማይችል አፅንኦት ለመስጠት ነው፡፡ ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል፡፡ “ሰዎች እኔን ለመጉዳት ምንም ማድረግ አይችሉም።”

እግዚአብሔር ረዳቴ ሆኖ ከአጠገቤ ነው

በአንድ ሰው አጠገብ መቆም ያንን ሰው ለመርዳት መወሰኑን የሚያመልክት ፈሊጣዊ አገላለፅ ነው። “እግዚአብሔር እኔን ለመርዳት ወስኖአል”

በሚጠሉኝ ሰዎች ላይ በድል አድራጊነት እመለከታለሁ

ይህ የሚያመለክተው ጸሐፊው እየተመለከተ ሳለ እግዚአብሔር ጠላቶቹን የሚያሸንፍለት እርሱ መሆኑን ነው፡፡ የዚህ ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊሆን ይችላል፡፡ “እግዚአብሔር የሚጠሉኝን ሁሉ ሲያሸንፋቸው አይቻለሁ”