am_tn/psa/116/012.md

1.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ይህን መዝሙር ያቀናበረው ሰው መናገሩን ይቀጥላል።

ስላደረገልኝ ሁሉ ... ለእግዚአብሔር ምን እመልሳለሁ?

ጸሐፊው ይህንን መሪ ጥያቄ የጠየቀው እግዚአብሔር ላደረገው ነገር እንዴት ምላሽ እንደሚሰጥ ለማስተዋወቅ ነው፡፡ ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል፡፡ “ላደረገልኝ ሁሉ ... ለእግዚአብሔር የምመልሰው እንዲህ ነው”

እኔ የመድኃኒትን ጽዋ አነሣለሁ

ይህ ምናልባት የሚያመለክተው ስለ መጠጥ ቁርባን ሲሆን ይህም ወይንን በመሠዊያው ላይ ማፍሰስን ይጠይቃል፤ ጸሐፊው ይህንን ቁርባን የሚያደርገው እግዚአብሔር ላደረገለት ማዳን ምላሽ እንዲሆን ነው፡፡ የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልፅ ሊደረግ ይችላል፡፡ “እርሱ ስላዳነኝ ለእግዚአብሔር የመጠጥ ቁርባንን አቀርባለሁ”

የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ

እዚህ ላይ “ስም” የሚለው ቃል እግዚአብሔርን ራሱን ይወክላል፡፡ “እግዚአብሔርን እጠራለሁ”