am_tn/psa/116/007.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ይህን መዝሙር ያቀናበረው ሰው መናገሩን ይቀጥላል።

ነፍሴ ወደ እረፍት ስፍራዋ መመለስ ትችላለች

ጸሐፊው ሰላምንና መተማመንን ማግኘት ልክ ነፍሱ የምታርፍበትን ስፍራ እንዳገኘች አድርጎ ይናገራል፡፡ “ነፍስ” የሚለው ቃል ግለሰቡን ይወክላል፡፡ “እንደገና በሰላም ማረፍ እችላለሁ”

አንተ ሕይወቴን ከሞት አዳንካት

እዚህ ላይ “እንተ” የሚለው ቃል እግዚአብሔርን ያመለክታል፡፡ “ሕይወት” የሚለው ቃል ግለሰቡን ይወክላል፡፡ “ከሞት አድነኸኛል” ወይም “ከመሞት ጠብቀኸኛል”

ዓይኖቼን ከእንባ

ትርጉሙን ግልፅ ለማድረግ የቃል ሐረግ ከቀዳሚው ሐረግ ሊወሰድ ይችላል፡፡ “ዓይኖቼን ከእንባ አዳንካቸው” ወይም “ከማልቀስ ጠብቀኸኛል”

እግሮቼን ከመሰናከል

ትርጉሙን ግልፅ ለማድረግ የቃል ሐረግ ከቀዳሚው ሐረግ ሊወሰድ ይችላል፡፡ እዚህ ላይ እግሮች ግለሰቡን ይወክላሉ፡፡ መሰናክል የሚለው ምናልባት በጠላቶቹ መገደልን ይወክላል፡፡ “ከመሰናክል አድነኸኛል” ወይም “በጠላቶቼ ከመገደል ጠብቀኸኛል”