am_tn/psa/116/003.md

1.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ይህን መዝሙር ያቀናበረው ሰው መናገሩን ይቀጥላል።

የሞት ገመዶች ከበቡኝ

ጸሐፊው ስለ ሞት የሚናገረው አንድን ሰው እንደ ያዘና በገመድ እንዳሰረው አድርጎ ነው፡፡ መዝሙር 18፡4ን እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት፡፡ “ልክ እንደምሞት ሆኖ ተሰማኝ”

የሲኦል ወጥመድ አገኘኝ

ጸሐፊው ስለ “ሲኦል” የሚናገረው የሙታን ስፍራ መሆኑን እና ልክ በወጥመድ እንደ ታያዘ ሰው አድርጎ ነው። “ልክ ወደ መቃብር ለመግባት ዝግጁ እንደሆንኩ ተሰማኝ”

የእግዚአብሔርንም ስም ጠራሁ

እዚህ ላይ “ስም” የሚለው ቃል የሚወክለው እግዚአብሔርን ራሱን ነው፡፡ “ወደ እግዚአብሔር ተጣራሁ”

ሕይወቴን አድናት

እዚህ ላይ “ሕይወት” የሚለው ቃል የሚወክለው ግለሰቡን ነው፡፡ “አድነኝ” ወይም “ከመሞት አድነኝ”