am_tn/psa/114/001.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ

በዕብራውያን የቅኔ አጻጻፍ ውስጥ ተመሳሳይነት የተለመደ አገላለጽ ነው፡፡

እስራኤል ከግብፅ ሲወጣ ያዕቆብም ባዕድ ቋንቋ ከሚናገሩ ሰዎች መካከል

እነዚህ ሁለቱ መስመሮች “እስራኤል” እና “የያዕቆብ ቤት” አንድ አይነት ትርጉም ያላቸው ናቸው፤ “ግብፅ” እና “የባዕድ አገር ሰዎች” የሚያመለክተው ስለ አንድ ሕዝብ ነው፡፡

የያዕቆብ ቤት ባዕድ ቋንቋ ከሚናገሩ ሰዎች

እዚህ ላይ “ቤት” የሚለው ቃል ቤተሰብን ወይም ዘሮችን ይወክላል፡፡ ግሱ ለዚህ ሐረግ ሊሆን ይችላል፡፡ “የያዕቆብ ዘሮች የማያውቁትን ቋንቋ ከሚናገሩ ሰዎች ትተው ወጡ”

ይሁዳ የተቀደሰ ስፍራው፣ እስራኤልም መንግሥቱ ሆነ

“ለይሁዳ” እና “እስራኤል” ተቀባይነት ያላቸው ትርጉሞች፦ 1) መሬቱን ያመለክታሉ፡፡ “የይሁዳ ምድር የእግዚአብሔር የተቀደሰ ስፍራ ሆነ፣ የእስራኤልም ምድር የእርሱ መንግሥት ሆነ” ወይም (2) እነርሱ ለይሁዳ እና ለእስራኤል ሕዝብ መገለጫዎች ናቸው፡፡ “የይሁዳ ሕዝብ እግዚአብሔር በመካከላቸው የሚኖር ሕዝብ ሆኑ፣ የእስራኤልም ሕዝብ ደግሞ የሚገዛበት ሆኑ”