am_tn/psa/110/005.md

1.9 KiB

ጌታ በቀኝህ ነው

ጌታ ወደ ጦርነት በሚሄድበት ጊዜ እግዚአብሔር ሊረዳው በቀኙ ይቆማል፡፡ “እግዚአብሔር በጦርነት ውስጥ ይረዳሃል”

ጌታ

“ጌታ” የሚለው ቃል እግዚአብሔርን ያመለክታል፡፡

እርሱ ይገድላል

“እርሱ” የሚለው ቃል እግዚአብሔርን ያመለክታል፡፡ ነገሥታቱ እንዲሸነፉና እንዲሞቱ ያደርጋል፣ ነገር ግን የንጉሡን ሠራዊት የጠላት ነገሥታትን እንዲገድሉ ይፈቅድላቸዋል፡፡ “ነገሥታቱን እንዲሞቱ ያደርጋል” ወይም “ሠራዊትህ ነገሥታትን እንዲገድሉ ይፈቅድላቸዋል”

ነገሥታት

ይህ ጠላቶቹን ይመለከታል፡፡ “ጠላቶች ነገሥታት”

በቊጣው ቀን

እዚህ ላይ ዳዊት እግዚአብሔር በሚቆጣበት ጊዜ ነገሥታትን በ“ቊጣው ቀን” እንደሚያሸንፋቸው ይናገራል፡፡ “ትዕግሥቱ ወደ ቊጣ በሚለወጥበት የፍርድ ቀን”

የጦርነት ሜዳዎችን በሬሳዎች ይሞላል

ይህ ማለት እግዚአብሔር ይህ እንዲሆን ያደርጋል፣ በጦር ሜዳ የሞቱትን ሰዎች ሁሉ እርሱ በግል ገድሏቸዋል ማለት አይደለም። “የጦር ሜዳዎቹን በሬሳዎች እንዲሞላ ያደርጋል”

እርሱ በብዙ አገሮች ውስጥ መሪዎችን ይገድላል

ይህ ማለት እግዚአብሔር ይህ እንዲሆን ያደርጋል፣ መሪዎቹን በግል ይገድላል ማለት አይደለም፡፡ “በብዙ አገሮች ውስጥ መሪዎችን እንዲገደሉ ያደርጋል” ወይም “በብዙ አገሮች ውስጥ መሪዎች እንዲሞቱ ይፈቅዳል”