am_tn/psa/110/002.md

1.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ዳዊት ለንጉሡ መናገሩን ቀጠለ።

እግዚአብሔር የኃይልህን በትር ይይዛል

ዳዊት እዚህ ላይ የሚናገረው እግዚአብሔር የንጉሡን የገዢነት በትሩን በመያዝ ግዛቱን እንደሚያሰፋለት ነው፡፡ “እግዚአብሔር በኃይል የምትገዛውን ስፍራ ያሰፋልሃል”

በጠላቶችህ መካከል ግዛ

“ንጉሥ፣ በጠላቶችህ መካከል ግዛ።” ይህ ለንጉሡ የተነገረው እንደ ትእዛዝ ነው፡፡

በራሳቸው ነፃ ፈቃድ

“በራሳቸው ምርጫ።” ይህ ማለት ንጉሡን ለመከተል ይመርጣሉ ማለት ነው፡፡

በኃይልህ ቀን

ይህ የሚያመለክተው ንጉሡ ሠራዊቱን ወደ ጦር ግንባር የሚመራበትን ቀን ነው። ይህ በግልጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ “ሠራዊትህን ወደ ጦርነት በምትመራበት ቀን”

ከንጋት ማኅፀን . . . እንደ ጠል

ዳዊት ጠልን ንጋት እንደሚወልደው ሕፃን ይገልጸዋል። “በማለዳ . . . እንደ ጠል”

ከንጋት ማኅፀን፣ ጎልማሳነትህ እንደ ጠል ልምላሜ ይሆንልሃል

ዳዊት ንጉሡን የሚናገረው በየጠዋቱ የሚኖረውን የወጣትነት ጥንካሬ በየቀኑ ማለዳ ከሚታየው ጠል ጋር በማነፃፀር ነው። “በየማለዳው ምድርን ለማለምለም የጠዋት ጤዛ እንደሚታይ አንተም ለመጽናት በወጣትነት ኃይል በየማለዳው ትሞላለህ”