am_tn/psa/110/001.md

1016 B

አጠቃላይ መረጃ

በዕብራውያን የቅኔ አጻጻፍ ውስጥ ተመሳሳይነት የተለመደ አገላለጽ ነው፡፡

የዳዊት መዝሙር

ተቀባይነት ያላቸው ትርጉሞች፦ 1) ዳዊት መዝሙሩን ጽፎአል ወይም 2) መዝሙሩ ስለ ዳዊት ነው ወይም 3) መዝሙሩ በዳዊት የመዝሙሮች አጻፋፍ ዘይቤ ነው፡፡

በቀኝ እጄ በኩል ተቀመጥ

“በቀኝ እጄ” የሚለው ሐረግ የሚያመለክተው የክብር ቦታን ነው፡፡ “ለአንተ ባለኝ የክብር ስፍራ ተቀመጥ”

ጠላቶችህን የእግርህ መርገጫ እስከማደርግልህ

እዚህ ላይ ዳዊት የሚገልጸው እግዚአብሔር የጌታን ጠላቶች በኃይሉ ቁጥጥር ስር አድርጎ ለእግሩ ልክ እንደ እግር መርገጫ እንደሚያደርግለት ነው፡፡ “ጠላቶችህን ከኃይልህ በታች አድርግ”