am_tn/psa/108/009.md

1020 B

አጠቃላይ መረጃ

እነዚህ ጥቅሶች በመዝሙር 60፡8-9 ካሉት ጋር ተመሳሳይ ናቸው፡፡

ሞዓብ መታጠቢያ ገንዳዬ ነው

እግዚአብሔር ስለ ሞዓብ አስፈላጊ እንዳልሆነ እንደ የመታጠቢያ ገንዳ ወይም ዝቅተኛ አገልጋይ እንደ ሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ “ሞዓብ ለመታጠቢያ እንደሚጠቀሙበት ሳህን ነው”

በኤዶምያስ ላይ ጫማዬን እወረውራለሁ

እግዚአብሔር ምናልባት የኤዶምያስ ላይ ያለውን ባለቤትነት በምሳሌነት ለመግለጽ ጫማውን ወደ ምድሩ በመወርወር የራሱ መሆኑን ያሳያል፡፡ የሆነ ሆኖ አንዳንድ ትርጉሞች ሌላ አይነት ትርጓሜ አሏቸው። “የኤዶምያስ ምድር ባለቤት ነኝ” ወይም “በኤዶምያስ ምድር የእኔ መሆኑን ለማሳየት ጫማዬን እጥላለሁ፣”