am_tn/psa/108/007.md

1.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ

እነዚህ ቁጥሮች በመዝሙር 60፡6-7 ካሉት ጋር ተመሳሳይ ናቸው፡፡

እግዚአብሔር በቅድስናው ተናግሯል

እዚህ ላይ ዳዊት የሚገልጸው እግዚአብሔር እርሱ ቅዱስ ስለሆነ በ“ቅድስናው” እንደሚናገር ነው፤ ልክ ቅድስናውን እርሱ በውስጡ እንዳለ ነገር አድርጎ ይገልጸዋል። “እግዚአብሔር እርሱ ቅዱስ ስለሆነ ተናግሯል”

ሴኬምን እከፍላለሁ እንዲሁም የሱኮትን ሸለቆ አካፍላለሁ

እዚህ ላይ እግዚአብሔር የሴኬምን ምድር ስለ መከፋፈል እንዲሁም የሱኮትን ሸለቆ ስለ ማካፈል ይናገራል፡፡

ማካፈል

በክፍሎች መከፋፈል

ኤፍሬም ደግሞ የራስ ቁሬ ነው

እግዚአብሔር የኤፍሬምን ነገድ የእርሱ ሰራዊት እንደ ሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ የራስ ቁር የጦር መሣሪያን ይወክላል። “ኤፍሬምን እንደ ራስ ቁር መርጬዋለሁ” ወይም “የኤፍሬም ነገድ ሠራዊቴ ነው”

የራስ ቁር

ወታደሮች ጭንቅላታቸውን ከጉዳት ለመጠበቅ የሚያደርጓቸው ጠንካራ ባርኔጣ

ይሁዳ በትሬ ነው

እግዚአብሔር ከይሁዳ ነገድ ወንዶችን በሕዝቡ ላይ ነገሥታት ይሆኑ ዘንድ መርጦአል፤ የሚናገረውም ስለእዚያ ነገድ እርሱም በትሩ እንደ ሆነ አድርጎ ነው፡፡ “የይሁዳ ነገድ እንደ በትሬ ነው” ወይም “ይሁዳ በእርሱ በኩል ሕዝቤን የምገዛበት በትር ነው”