am_tn/psa/108/003.md

994 B

የቃል ኪዳንህ ታማኝነት ከሰማያት በላይ ታላቅ ነው፤ ታማኝነትህ እስከ ሰማይ ይደርሳል

እነዚህ ሁለት ሐረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ የሚናገሩት የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታማኝነት እና አስተማማኝነት ልክ እንደ አንድ ቁመቱ እስከ ሰማይ እንደሚደርስ ረጅም ነገር ታላቅ መሆኑን በመጥቀስ ነው። “ታማኝነት” እና “አስተማማኝነት” የሚሉት ረቂቅ ስሞች እንደ ቅፅል ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡ “የቃል ኪዳን ታማኝነትህ እና አስተማማኝነትህ ከመሬት እስከ ሰማይ እንዳለ ርቀት ታላቅ ነው” ወይም “አንተ ለቃል ኪዳንህ የበለጠ ታማኝ ነህ፣ እንዲሁም ሰዎች ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል በአንተ ሊታመኑብህ የሚገባ ነህ”