am_tn/psa/107/031.md

1.1 KiB

ኦ እነዚያ ሰዎች ስለ እግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታማኝነቱ ሊያመሰግኑት ይገባል

እዚህ ላይ “ኦ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሰዎች እግዚአብሔርን እንዲያመሰግኑ ጠንከር ያለ ማሳሰቢያ መስጠትን ነው፡፡ “ታማኝነት” የሚለው ረቂቅ ስም ከቅፅል ጋር ሊተረጎም ይችላል፡፡ ይህንን በመዝሙር 107፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት፡፡ “እርሱ ለቃል ኪዳኑ ታማኝ ስለ ሆነ ሕዝቡ እግዚአብሔርን ያመስግኑ” ወይም “ሕዝቡ እግዚአብሔርን ማመስገን ያለባቸው እርሱ ለቃል ኪዳኑ ታማኝ ስለሆነ ነው”

በሽማግሌዎች ሸንጎ ይወድሱት

“ሽማግሌዎች በአንድ ላይ ሲቀመጡ።” ሽማግሌዎች በኅብረተሰቡ መካከል ያለውን ጉዳይ ለመነጋገርና ውሳኔዎችን ለመስጠት በአንድነት ተቀምጠዋል፡፡