am_tn/psa/107/020.md

1.1 KiB

ቃሉን ላከ ፈወሳቸውም

እዚህ ላይ ዳዊት የሚገልጸው እግዚአብሔር ቃሎቹን እንደ መልእክተኛ ልኮ እንደሚናገር ነው፡፡ ተቀባይነት ያላቸው ትርጉሞች 1) “እንዲፈወሱ አዘዘ እነርሱም ተፈወሱ” ወይም 2) “አበረታታቸው ፈወሳቸውም”

ኦ እነዚያ ሰዎች ስለ እግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታማኝነቱ ሊያመሰግኑት ይገባል

እዚህ ላይ “ኦ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሰዎች እግዚአብሔርን እንዲያመሰግኑ ጠንከር ያለ ማሳሰቢያ መስጠትን ነው፡፡ “ታማኝነት” የሚለው ረቂቅ ስም ከቅፅል ጋር ሊተረጎም ይችላል፡፡ ይህንን በመዝሙር 107፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት፡፡ “እርሱ ለቃል ኪዳኑ ታማኝ ስለ ሆነ ሕዝቡ እግዚአብሔርን ያመስግኑ” ወይም “ሕዝቡ እግዚአብሔርን ማመስገን ያለባቸው እርሱ ለቃል ኪዳኑ ታማኝ ስለሆነ ነው”