am_tn/psa/107/011.md

1.9 KiB

በእግዚአብሔር ቃል ላይ አመፁ . . . የልዑሉንም ትእዛዝ አንቀበልም አሉ

እነዚህ ሐረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አሏቸው ትኩረት የሚሰጡትም ምን ያህል በእግዚአብሔር ላይ እንዳመፁ ነው፤ ለዚህም ነው በእስር ቤት የተጣሉት፡፡

በመከራ ጊዜ ልባቸውን ትሑት አደረገ

እዚህ ላይ ልብ የሚለው አንድን ሰው ይወክላል፣ ነገር ግን በተወሰነ ሁኔታ ፈቃዱን የሚያመለክት ነው፡፡ “መከራ እንዲቀበሉ በማድረግ ትሑት እንዲሆኑ አደረጋቸው”

ችግር

  1. “መከራ” ወይም 2) “ከባድ ሥራ” የሚሉት ትርጉሞችም ተቀባይነት አላቸው፡፡

ተሰናከሉ፤ የሚረዳቸውም አልነበረም

“ተሰናከሉ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው እነዚህ ሰዎች እጅግ አስቸጋሪ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ የነበሩባቸውን ጊዜያት ነው፡፡ “መከራ ውስጥ ገቡ ማንም ከመከራ ውስጥ እንዲወጡ የሚረዳቸው አልነበረም”

በመከራቸውም ወደ እግዚአብሔር ጮኹ

ይህም ማለት እግዚአብሔር እንዲረዳቸው ወደ እርሱ ጸለዩ ማለት ነው፡፡ ይህንን በመዝሙር 107:6 እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት፡፡ “በመከራቸው እንዲረዳቸው ወደ እግዚአብሔር ጸለዩ”

ጭንቀታቸው

“ችግር” ወይም “ሥቃይ።” ይህንን በመዝሙር 107፡6 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት

አመጣ

እዚህ ላይ ዳዊት እግዚአብሔር ከጭንቀታቸው እንዳዳናቸው ጭንቀታቸውንም እርሱ እነርሱን አድኖ እንዳመጣበት ተጨባጭ ስፍራ አድርጎ ይገልጸዋል።