am_tn/psa/107/008.md

1.7 KiB

ኦ እነዚያ ሰዎች ስለ እግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታማኝነቱ ሊያመሰግኑት ይገባል

እዚህ ላይ “ኦ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሰዎች እግዚአብሔርን እንዲያመሰግኑ ጠንከር ያለ ማሳሰቢያ መስጠትን ነው፡፡ “ታማኝነት” የሚለው ረቂቅ ስም ከቅፅል ጋር ሊተረጎም ይችላል፡፡ “እርሱ ለቃል ኪዳኑ ታማኝ ስለ ሆነ ሕዝቡ እግዚአብሔርን ያመስግኑ” ወይም “ሕዝቡ እግዚአብሔርን ማመስገን ያለባቸው እርሱ ለቃል ኪዳኑ ታማኝ ስለሆነ ነው”

ለሰብአዊነት

“ለሁሉም ሰዎች”

እርሱ የተጠሙትን ሰዎች ፍላጎት አርክቶአል

“ለሚፈልጉት ውሃን ሰጣቸው፣ ለተጠሙትም”

የተራቡትን ሰዎች ፍላጎት በመልካም ነገሮች አጥግቦአል

“እጅግ ለተራቡ እና ምግብ ላስፈለጋቸው፣ ይበሉ ዘንድ መልካምን ነገር ሰጣቸው”

አንዳንዶች ተቀመጡ

ይህ የሚያመለክተው እነዚህ ሰዎች እግዚአብሔር ያዳናቸው መሆናቸውን ነው፡፡ “እግዚአብሔር የተቀመጡትን ሰዎች አድኖአቸዋል”

በጨለማ እና በድንግዝግዝ ውስጥ

“ጨለማ” እና “ድንግዝግዝ” በመሠረቱ አንድ አይነት ትርጉም ያላቸው ሲሆኑ የነበሩበት ስፍራ ምን ያህል ጨለማ እንደነበረ ትኩረት ለመስጠት ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ “በፍጹም ጨለማ ውስጥ”