am_tn/psa/107/001.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ

በዕብራውያን የቅኔ አጻጻፍ ውስጥ ተመሳሳይነት የተለመደ አገላለጽ ነው፡፡

የቃል ኪዳኑ ታማኝነት ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል

“ታማኝነት” የሚለው ረቂቅ ስም ከቅፅል ጋር ሊተረጎም ይችላል፡፡ “ለቃል ኪዳኑ ለዘላለም ታማኝ ነው”

እግዚአብሔር የተቤዣቸው

“የተቤዣቸው” የሚለው ቃል የሚያመለክተው እግዚአብሔር ያዳናቸውን ሰዎች ነው። “እነርሱ እግዚአብሔር ያዳናቸው”

መናገር

ይህ ማለት ስለ አንድ ነገር ለሌሎች መናገር ማለት ነው፡፡ “እግዚአብሔር ስላደረገው ነገር ተናገሩ”

ከጠላት እጅ

እዚህ ላይ “እጅ” የሚለው የሚያመለክተው ኃይልን ነው፡፡ “ከጠላት ኃይል”

ከምሥራቅ . . . እና ከደቡብ

እዚህ ላይ አራቱ አቅጣጫዎች ትኩረት የተሰጣቸው ከሁሉም ስፍራ እንደ ሰበሰባቸው ለማመልከት ነው። “ከሁሉም አቅጣጫ” ወይም “ከሁሉም የዓለም ክፍል”

ከምሥራቅና ከምዕራብ፣ ከሰሜን እና ከደቡብ

ይህ የሚገልጸው እግዚአብሔር ሕዝቡን የሚሰበስበባቸውን ስፍራዎች ነው፡፡ “እርሱ ከምሥራቅና ከምዕራብ፣ ከሰሜን እና ከደቡብ ሰበሰባቸው”