am_tn/psa/106/016.md

1.2 KiB

በሰፈር ውስጥ

ይህ በምድረ በዳ የሚገኘውን የእስራኤል ሰፈር ያመለክታል፡፡ “በምድረ በዳ ሰፈር ውስጥ”

ምድር ተከፍታ ዋጠቻቸው

እዚህ ላይ ምድር ተከፍታ ሰዎችን መቅበሯ ፍጥረት አንድ ነገር ከመዋጡ ጋር ይነጻጸራል፡፡ “ምድር ተከፈተች ቀበረቻቸውም”

ዳታን

ይህ በሙሴ ላይ ያመፀ የታወቀ ሰው ነበር፡፡

የአቢሮን ተከታዮች ተሸፈኑ

የአቢሮን ተከታዮችም መሬቷ ተከፍታ ዳታንን ስትቀብረው አብረው ተቀብረዋል፡፡ “የአቢሮን ተከታዮች ተሸፍነዋል” ወይም “የአቢሮን ተከታዮች ተቀብረዋል”

አቢሮን

ይህ በሙሴ ላይ ያመፀ የታወቀ ሰው ነበር፡፡

እሳት በመካከላቸው ተነሣ፤ ክፉዎችን በላች

እነዚህ ሁለት ሐረጎች ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆን፣ ክፉ ሰዎች በእሳት እንዴት እንደ ተገደሉ አጽንኦት ለመስጠት በአንድነት ተጽፈዋል፡፡