am_tn/psa/105/043.md

1.3 KiB

ሕዝቡን መራቸው . . . የመረጣቸውንም በድል አድራጊነት ድምፅ

እነዚህ ሁለቱ ሐረጎች በመሠረቱ ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆኑ፣ እግዚአብሔር ሕዝቡን ከግብፅ አውጥቶ በመራቸው ጊዜ ደስተኞች እንደ ነበሩ አጽንኦት ለመስጠት በአንድነት ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ ሕዝቡ በደስታ ይጮኹ ነበር፡፡ “የተመረጡትን ሕዝቦቹን በደስታ እና በድል አድራጊነት ድምፅ መራቸው”

የመረጣቸው

እዚህ ላይ “የመረጣቸው” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የእግዚአብሔርን የተመረጠ ሕዝብ ነው፡፡ “የእርሱ የተመረጠ ሕዝብ”

የድል አድራጊነት ድምፅ

ጠላቶቻቸውን ስላሸነፉ ሕዝቡ በደስታ የሚያሰሙት የድል አድራጊነት ድምፅ ነው

ሥርዓቱን ጠብቁ ሕጎቹን ታዘዙ

እነዚህ ሁለት ሐረጎች በመሠረቱ አንድ ዓይነት ትርጉም አላቸው፣ አጽንኦት ለመስጠት ግን በአንድነት ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ ሥርዓቱን “መጠበቅ” ማለት እነርሱን መታዘዝ ማለት ነው፡፡ “ሕጉንና ሥርዓቱን መታዘዝ”