am_tn/psa/105/024.md

1.1 KiB

እግዚአብሔር ሕዝቡን ፍሬያማ አደረጋቸው

ጸሐፊው የእስራኤልን መብዛት ብዙ ፍሬ እንዳፈራ ተክል አድርጎ ገልጾታል፡፡ “እግዚአብሔር የሕዝቡን ቁጥር እጅግ አበዛው”

ሕዝቡን ለመጥላት፣ አገልጋዮቹንም ለመበደል

“ሕዝቡን ለመጥላት እና አገልጋዮቹን ለመበደል”

ምልክቶቹን በግብፃውያን መካከል አደረጉ ... ተአምራቱንም በካም ምድር

እነዚህ ሁለቱ ሐረጎች በመሠረቱ ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ “ሙሴና አሮን የእግዚአብሔርን ተአምራት በግብፅ ውስጥ በካም ዝርያዎች መካከል አደረጉ”

ድንቆቹን በካም ምድር

“አደረጉ” የሚለው ቃል ቀደም ሲል በነበረው ሐረግ ውስጥ ግንዛቤ ተገኝቶበታል፡፡ እዚህም ላይ በድጋሚ ሊገለጹ ይችላሉ፡፡ “ድንቆቹንም በካም ምድር አደረጉ”