am_tn/psa/104/013.md

1.1 KiB

በሰማይ ካለው የውሃ እልፍኙ ተራሮችን ውሃ ያጠጣል

ይህ ማለት እግዚአብሔር ዝናብ ያዘንባል ማለት ነው፡፡ ውሆች የተገለጹት በሰማይ ባለው እልፍኝ እንደሚኖሩ ተደርጎ ነው፡፡ "እርሱ ዝናብ ከሰማይ እንዲዘንብ በማድረግ ተራሮችን ውሃ ያጠጣል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የእርሱ የስራ ፍሬ

"አንተ የፈጠርካቸው ብዙ መልካም ነገሮች"

ሰው እንዲንከባከባቸው ዕፅዋትን ታበቅላለህ

"እርሱ አደረገ" እና "በቀሉ" የሚሉት ቃላት በቀደመው ሀረግ ወስጥ በውስጠ ታዋቂነት ይገኛሉ፣ እናም እዚህ ስፍራ ሊደገሙ ይችላሉ፡፡ "እርሱ ሰው እንዲንከባከባቸው ተክሎች እንዲበቅሉ ያደርጋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የተተወ/የተዘለለ የሚለውን ይመልከቱ)