am_tn/psa/104/006.md

1.3 KiB

አንተ ምድርን እንደ ልብስ በውሃ ሸፈንክ

እዚህ ስፍራ ምድርን የሸፈነው ውሃ የተነጻጸረው ትልቅ ልብስ አንድን ነገር እንዴት ሙሉ ለሙሉ እንደሚሸፍን ከዚያ ጋር ነው፡፡ "አንተ ምድርን ሙሉ ለሙሉ በውሃ ሸፈንክ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የአንተ ግሳጼ ውሆችን…እነርሱም ይሸሻሉ

እነዚህ ሁለት ሀረጎች በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው ደግሞም በአንድነት የዋሉት እግዚአብሔር እንዴት እንደተናገረ እና ውሆች እንደሸሹ ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ይመለሳሉ

ወደ ኋላ መመለስ፣ ዝቅ ማለት

ይሸሻሉ

እዚህ ስፍራ ዘማሪው ስለ ውሆች መመለስ የሚናገረው የያህዌን ድምጽ ከሰሙ በኋላ ልክ እንደ አንስሳ እንደሚሸሹ አድርጎ ነው፡፡ "መሸሽ" የሚለው ቃል በፍጥነት መሮጥ ማለት ነው፡፡ "በችኮላ መሸሽ/ፈጥኖ መሄድ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)