am_tn/psa/104/004.md

1.2 KiB

እርሱ ነፋሳትን መልዕክተኞቹ አደረገ

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) እርሱ ነፋስ እንደ መልዕክተኛ መልዕክት እንዲያደርስ አደረገ፣ "እርሱ ነፋሳትን መልዕክተኞቹ አደረገ" ወይም 2) "እርሱ መልዕክተኞቹን እንደ ነፋስ ፈጣን አደረገ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

የእሳት ነበልባልን አገልጋዮቹ

ይህ በቀደመው ዐረፍተ ነገር ውስጥ በውስጠ ታዋቂነት ከቀረበው መረጃ ጋር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "እርሱ የእሳት ነበልባልን አገልጋዮቹ አደረገ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የተተወ/የተዘለለ የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ የምድር መሰረቶችን መሰረተ

እዚህ ስፍራ "መሰረቶችን መሰረተ" የሚለው ሀረግ "ፈጠረ" ማለት ነው፡፡ "እርሱ መላዋን ምድር ፈጠረ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)