am_tn/psa/104/001.md

3.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ በዕብራውያን ስነግጥም ውስጥ የተለመደ ነው፡፡ (ስነ ግጥም እና ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

አጠቃላይ መረጃ፡

ይህ ዝማሬ የውዳሴ መዝሙር ነው

በሙሉ ህይወቴ

የዚህ ሀረግ ትርጉም ያህዌን በሙሉ ልቡ ያወድሰዋል ደግሞም ለእርሱ ላለው መሰጠት ትኩረት ይሰጣል ማለት ነው፡፡ "በሙሉ ማንነቴ" ወይም "በሙሉ ነፍሴ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ውበትን እና ግርማዊነትን ለብሰሃል

"ውበት" እና "ግርማ" የሚሉት ቃላት ተመሳሳይ ትርጉም ሲኖራቸው ለያህዌ ክብር ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ የተገለጹትም ያህዌ እንደ ልብስ እንደተጎናጸፋቸው ተደርጎ ነው፡፡ "በአንተ ዙሪያ ውበት እና ግርማ አለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

አንተ ራስህን እንደ ልብስ በብርሃ ሸፍነሃል

ያህዌ የተገለጸው ብርሃን እንደ ልብስ በዙሪያው እንደሸፈነው ተደርጎ ነው፡፡ "አንተ በብርሃን ተሸፍነሃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አንተ ሰማያትን እንደ ድንኳን መጋረጃ ዘርግተሃል

እዚህ ስፍራ እግዚአብሔር የተገለጸው ሰው በውስጡ የሚቀመጥበት መጋረጃ እንደሚዘረጋ፣ ያህዌ ሰማያትን እንደ ዘረጋ ተደርጎ ነው፡፡ "ሰው ድንኳን እንደሚዘረጋ አንተ ሰማያትን ዘረጋህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የአዳራሽህን አግዳሚ በደመናት ላይ ዘረጋህ

"አንተ ላይኛውን ክፍልህን በሰማያት ገነባህ፡፡" ይህ የሚያመለክተው የእርሱ ቤት የላይኛው ወለል እጅግ ረጅም ከመሆኑ የተነሳ እስከ ደመናት እንደሚደርስ ነው፡፡

አንተ ደመናትን ሰረገላህ አደረግህ

እዚህ ስፍራ ደመናት የተገለጹት ሰረገላ ሆነው ያህዌን እንደተሸከሙ ተደርጎ ነው፡፡ "አንተ ደመናት እንደ ሰረገላ እንዲሸከሙህ አደረግህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

አንተ በነፋሳት ክንፎች ላይ ትራመዳለህ

እዚህ ስፍራ የነፋስ መንፈስ የተገለጸው ያህዌ እንደሚራመድባቸው ክንፎች ተደርጎ ነው፡፡ "አንተ በነፋስ ላይ ትራመዳለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)