am_tn/psa/103/014.md

2.2 KiB

እኛ እንዴት እንደተሰራን/እንደተበጀን

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "የእኛ አካል የሚመስለው" ወይም "እርሱ አካላችንን ያበጀው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

እርሱ አፈር መሆናችንን ያውቃል

ያህዌ የመጀመሪያውን ሰው አዳምን ሲፈጥር፣ የፈጠረው ከአፈር ነው፡፡ "እርሱ ከአፈር እንደ ፈጠረን ያውቃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ሰው ቀናቱ እንደ ሳር ነው

በዚህ ንጽጽር፣ የሰው ህይወት ዘመን መጠኑ የተወዳደረው ሳር ከመጠውለጉ አስቀድሞ ከሚኖራት አጭር ጊዜ ጋር ነው፡፡ "የሰው የህይወት ዘመን እንደ ሳር እድሜ አጭር ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ ሜዳ አበባ ያብባል

በዚህ ንጽጽር፣ ሰው እንዴት በጊዜ ውስጥ እንደሚያድግ የተወዳደረው ከአበባ እድገት ጋር ነው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ያብባል

"ማበብ" በሚገባ ወይም ውብ ሆኖ ማደግ ነው፡፡

ነፋስ በላዩ ይነፍሳል፣ ከዚያም ይጠፋል…በቅሎበት ከነበረው ስፍራ

እነዚህ ሀረጋት ስለ አበቦች እና ሳር መናገራቸውን ይቀጥላሉ፡፡ አበቦች እና ሳር እንዴት እንደሚሞቱ ከሰው አሟሟት ጋር ያነጻጽራሉ፡፡ "ነፋስ በአበቦች እና ሳሮች ላይ ይነፍሳል፣ እነርሱም ይጠፋሉ፤ ማንም የት ስፍራ በቅለው እንደነበር መናገር አይችልም - የሰው ልጅም እንደዚሁ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)