am_tn/psa/101/007.md

1.7 KiB

አስመሳይ ሰዎች…ሀሰተኛ ሰዎች

እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ሀሳብ ሲኖራቸው በአንድነት የዋሉት ዳዊት አስመሳዮችን እንደማይታገስ ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ሀሰተኞች ተቀባይነት የላቸውም

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ሀሰተኞችን አልቀበላቸውም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

በዐይኖቼ ፊት

እዚህ ስፍራ "የእኔ ዐይኖች" የሚለው የሚያመለክተው ራሱን ዳዊትን ነው፡፡ "በእኔ ፊት" ወይም "እኔ በምገኝበት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

በየማለዳው

"በየዕለቱ)

ክፉዎች

ይህ የሚያመለክተው ክፉ ሰዎችን ነው፡፡ "ክፉ ሰዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስማዊ ቅጽሎች የሚለውን ይመልከቱ)

ከያህዌ ከተማ

ዳዊት እርሱ የሚገኝበትን ከተማ "የያህዌ ከተማ" በማለት ይጠራታል፡፡ይህ ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ "የያህዌ ከተማ ከሆነችው፣ ከዚህች ከተማ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)