am_tn/psa/101/004.md

1.6 KiB

ለክፉ

"ክፉ ለሆነ ማናቸውም ነገር"

በትዕቢት የሚያዋርድ እና እብሪተኛ ዝንባሌ

እነዚህ ሁለት ሀረጎች በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም ሲኖራቸው እንዲህ አይነት ሰዎች እንዴት እንደሚታበዩ ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

በትዕቢት የሚያዋርዱ

"በግልጽ የሚታይ ትዕቢት፡፡" ይህ ትዕቢቱን ማንም በግልጽ ሊመለከተው ስለሚችለው ሰው ይናገራል፡፡

ትሁቱ ከጎኔ እንዲቀመጥ አደርጋለሁ

ይህ ማለት ዳዊት እንዲህ ያሉ ሰዎች በእርሱ ዙሪያ እንዲሆኑ እና ከእርሱ ጋር እንዲኖሩ ይፈቅዳል፡፡ "በምድሪቱ የሚገኙ ታማኝ ሰዎች ከእኔ ጋር እንዲኖሩ እፈቅዳለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ታማኞች

ይህ ለእግዚአብሔር ታማኝ የሆኑ ሰዎችን ያመለክታል፡፡ "ታማኝ ሰዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስማዊ ቅጽሎች የሚለውን ይመልከቱ)

በአንድነት መንገድ የሚራመዱ

እዚህ ስፍራ ዳዊት ስለ "መኖር" የሚናገረው "መራመድ" እንደሆነ አድርጎ ነው፡፡ "ሀቀኛ እና ትክክለኛ በሆነ መንገድ መኖር" ወይም "በሀቅ የተሞላ ህይወትን መኖር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)