am_tn/psa/101/002.md

2.2 KiB

በአንድነት መንገድ እሄዳለሁ

እዚህ ስፍራ ዳዊት ስለ "መኖር" የሚናገረው "መራመድ" እንደሆነ አድርጎ ነው፡፡ "እውነተኛ እና ትክክለኛ በሆነ መንገድ እኖራለሁ" ወይም "አንድነት/ሀቀኝነት የተሞላ ህይወትን እኖራለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በቤቴ ውስጥ በአንድነት/ሀቀኝነት እራመዳለሁ

እዚህ ስፍራ ዳዊት ስለ "መኖር" የሚናገረው መኖር "መራመድ" እንደሆነ አድርጎ ነው፡፡ ዳዊት አንድነትን በቤቱ ውስጥ ተወስኖ እንደሚኖር አካላዊ ቁስ አድርጎ ቢመለከትም፣ ቤቱን በአንድነት እንደሚቆጣጠር ይናገራል፡፡ "ቤቴን በአንድነት/በሀቀኝነት እቆጣጠራለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በዐይኖቼ ፊት ትክክለኛ ያልሆኑ ስራዎችን አላኖርም

"ትክክለኛ ያልሆኑ" የሚለውን ረቂቅ ስም ዳግም ማስተካከል ይቻላል፡፡ "ክፉ የሆነውን በዐይኖቼ ፊት ማኖር፣" የሚለው ፈሊጥ ትርጉም ይህ ማረጋገጥ ማለት ነው፡፡ "እኔ ባለሁበት ለማናቸውም ትክክለኛ ያልሆነ ድርጊት ለሚፈጽም ይሁንታ አልሰጥም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች እና ፈሊጣዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

በእኔ ላይ አይጣበቅም

ዳዊት "ክፉውን" በእርሱ ላይ ሊጣበቅ እንደማይችል ነገር አድርጎ ይናገራል፡፡ ይህም ማለት ክፉ ነገሮች እና ሰዎች ክፉ እንዳያደርጉ ይከለክላቸዋል ማለት ነው፡፡ "ክፉውን ፍጹም አስወግደዋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

መጣበቅ

ከአንድ ነገር ወይም ከአንድ ሰው ጋር በጣም በጥብቅ መያያዝ