am_tn/psa/099/001.md

2.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ በዕብራውያን ስነግጥም ውስጥ የተለመደ ነው፡፡ (ስነ ግጥም እና ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

አገራት

ይህ የሁሉንም አገራት ሰዎች ያመለክታል፡፡ "የሁሉም አገራት ሰዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

መናወጥ

በፍርሃት መንቀጥቀጥ

እርሱ ከኪሩቤል በላይ በዙፋኑ ተቀምጧል

ኪሩቤል በቃል ኪዳኑ ታቦት መክደኛ ላይ የሚገኙ መሆኑን ግልጽ ማድረግ ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፍት ብዙወን ጊዜ ስለ ቃል ኪዳኑ ታቦት፣ የያህዌ በላይ በሰማይ ተቀምጦ የቃል ኪዳኑ ታቦት የእግሩ ማረፊያ እንደሆነ አድርገው ይገልጻሉ፡፡ "እርሱ በዙፋኑ ላይ ከኪሩቤል በላይ በቃል ኪዳኑ ታቦት ተቀምጧል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ተናወጠ

ተንቀጠቀጠ

ያህዌ በጽዮን ታላቅ ነው፤ እርሱ ከአገራት ሁሉ በላይ ከፍ ብሏል

"ያህዌ ታላቅነቱ በጽዮን ብቻ አይደለም፣ በአገራት ሁሉ ላይ እርሱ ከፍ ያለ ነው" ወይም "ያህዌ የሚገዛው በጽዮን ላይ ብቻ አይደለም፣ እርሱ በአገራት ሁሉ ላይ ይገዛል"

እርሱ በአገራት ሁሉ ላይ ከፍ ያለ ነው

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "በሁሉም አገራት የሚኖሩ ሰዎች እርሱን ከፍ ያደርጉታል" ወይም "የአገራት ሁሉ ህዝቦች በታላቅ ሁኔታ ያወድሱታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ እና ተደራጊ እንደዚሁም ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ)

ታላቁን እና አስደናቂ ስምህን ያወድሱ

እዚህ ስፍራ ጸሐፊው ስለ እግዚአብሔር ከመናገር፣ ለእግዚአብሔር ወደ መናገር ዘወር ይላል፡፡ በእርግጥ ከዚህ ሀረግ በኋላ ዳግም ተመልሶ ስለ እግዚአብሔር ይናገራል፡፡