am_tn/psa/098/007.md

1.9 KiB

ባህር እና በውስጡ የሚገኘው ሁሉ እልል ይበል

ዘማሪው ባህርን ወደ እግዚአብሔር እንደ ሚጮህ ሰው አድርጎ ይገልጸዋል፡፡ "ባህር እና በውስጡ የሚገኘው ሁሉ እልል ይበሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ዓለም እና በውስጧ የሚኖሩ ሁሉ

ዘማሪው የሚነገረው ዓለም ሰው እንደሆነች አድርጎ ነው፡፡ "እናም ዓለም እና በውስጧ የሚኖሩ ሁሉ እልል ይበሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የተተወ/ የተዘለለ እና ሰውኛ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

ወንዞች በእጆቻቸው ያጨብጭቡ፣ ደግሞም ተራሮች በደስታ እልል ይበሉ

ዘማሪው ወንዞች እና ተራሮች ማጨብጨብ እና እልል ማለት እንደሚችሉ አድርጎ ይናገራል፡፡ "ወንዞች ማጨብጨብ እንደሚችሉ እና ተራሮች በደስታ እልል ማለት እንደሚችሉ ይሁኑ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ዓለም… አገራት

እነዚህ ሀረጎች "በዓለም ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች" እና "በአገራት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች" ሜቶኖሚ ናቸው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

አገራት በትክክለኝነት

ግሱ ከቀደመው ሀረግ ሊወሰድ ይችላል፡፡ "እርሱ አገራትን በትክክል ይዳኛል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የተተወ/ የተዘለለ የሚለውን ይመልከቱ)

በትክክለኝነት

"በእውነተኝነት" ወይም "ያለ አድልኦ"