am_tn/psa/097/009.md

3.9 KiB

ከሁሉ በላይ ከፍ ያሉ ናቸው

ዘማሪው ለመግዛት በጣም ጠንካራ የሆኑት በአካል ኬሎቹ ከፍ ያሉ እንደሆኑ አድርጎ ይናገራል፡፡ "በዚያ ከሚኖሩ ሰዎች በላይ ሆነው የሚገዙ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ)

አንተ እሰከ ሩቅ ከፍ ብለሃል

ዘማሪው ለመግዛት በጣም ጠንካራ የሆኑት በአካል ኬሎቹ ከፍ ያሉ እንደሆኑ አድርጎ ይናገራል፡፡ "አንተ እስከ ሩቅ ከፍ ያልክ ነህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ ከክፉዎች እጅ ያስጥላቸዋል

"እጅ" የሚለው ቃል የሚወክለው ሀይልን ነው፡፡ ያህዌ ሰዎችን ከክፉዎች ሀይል ማዳኑ የተገለጸው ከእጃቸው እንደሚወስዳቸው/እንደሚያስጥላቸው ተደርጎ ነው፡፡ "እርሱ ከክፉዎች ሀይል ያድናቸዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

ብርሃን ለ…ይዘራል፣ ደስታ ደግሞ ለ…

እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፣ ደግሞም ትኩረት ለመስጠት በእንድነት ቀርበዋል፡፡ "ያህዌ ትክክለኛ ስራ ለሚሰሩ ብርሃን ያወጣላቸዋል/ይዘራል፤ እውነተኛ ልብ ላላቸው ደስታን ይጨምርላቸዋል/ይዘራል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ እንደዚሁም የተተወ/የተዘለለ የሚሉትን ይመልከቱ)

ለጻድቃን ብርሃን ይወጣላቸዋል/ይዘራል

"መውጣት/መዝራት" የሚለው ቃል ወደፊት ውጤቱ ለሚታወቅ ነገር ዘይቤያዊ አነጋገር ነው፡፡ "ብርሃን" ለመልካም ነገር ዘይቤ ነው፡፡ "ያህዌ ለጻድቃን መልካም እንደሚሆን ያስባል/ያቅዳል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ጻድቃን

"ጻድቅ" የሚለው ቅጽል በስማዊ ሀረግ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ጻድቅ ሰዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስማዊ ቅጽል የሚለውን ይመልከቱ)

ሀቀኛ/ትክክለኛ ልብ ላላቸው ደስታ ይሆናል

"ይዘራል/ይሆናል" የሚለው ቃል በውስጠ ታዋቂነት አለ፡፡ "መዝራት" የሚለው ቃል ወደፊት ውጤቱ ለሚታወቅ ነገር ዘይቤያዊ አነጋገር ነው፡፡ "ደስተኛነት" የሚለው ረቂቅ ስም "ደስታ" ተብሎ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ደስተኝነት ሀቀኛ ልብ ላላቸው ይዘራል" ወይም "ያህዌ ሀቀኛ ልብ ያላቸው ወደፊት ደስተኛ ይሁኑ ዘንድ ያቅዳል/ያስብላቸዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የተተወ/የተዘለለ እና ዘይቤያዊ አነጋገር እንደዚሁም ረቂቅ ስሞች የሚሉትን ይመልከቱ)

ሀቀኛ ልብ ያላቸው

ልብ ለሰው ጠቅላላ ማንነት ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ/ ነው፡፡ "ሀቀኛ ሰዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)