am_tn/psa/097/003.md

1.3 KiB

እሳት በፊቱ ይሄዳል

ዘማሪው እሳትን ከንጉሡ ያህዌ ፊት እንደሚሄድ ሰው እንደሆነ አድርጎ ይገልጻል፤ ደግሞም ለሰዎች ንጉሡ እየመጣ እንደሆነ ይናገራል፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ተቃዋሚዎቹን ይበላል

"ጠላቶቹን ያቃጥላል"

ምድር ተመለከተች ተንቀጠቀጠችም

ጸሐፊው ስለ ምድር ያህዌ የሚያደርገውን የምትመለከት ሰው እንደሆነች እና በፍርሃት እንደምትንቀጠቀጥ አድርጎ ይገልጻታል፡፡ "ምድር እንደ ሰው ትመለከታለች ደግሞም ትንቀጠቀጣለች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ተናወጠች

ከፍርሃት የተነሳ መንቀጥቀጥ

ተራሮች በያህዌ ፊት እንደ ሰም ይቀልጣሉ

ጸሐፊው ተራሮች በያህዌ ፊት እሳት ፊት እንዳለ ሰም እንደሚቀልጡ ይናገራል፡፡ "ተራሮች ያህዌ ሲቀርባቸው በፊቱ ሊቆሙ አይችሉም" ወይም "ተራሮች በያህዌ መገኘት ይወድቃሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)