am_tn/psa/093/001.md

2.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ በዕብራውያን ስነግጥም ውስጥ የተለመደ ነው፡፡ (ስነ ግጥም እና ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

ክብርን ተጎናጽፏል፤ ያህዌ ክብርን ለብሷል ብርታትንም ታጥቋል

ዘማሪው ስለ ያህዌ ጥንካሬ እና ክብር የሚናገረው ያህዌ እነዚህን ነገሮች እንደለበሳቸው አድርጎ ነው፡፡ "እርሱ ለእያንዳንዱ ሀያል ንጉሥ መሆኑን ያሳያል" ወይም "ግርማዊነቱን፣ ንጉሥ እንደሚጎናጸፈው ካባ ሁሉም ይመለከተዋል፤ ሁሉም ነገር የያህዌን ብርታት እና እርሱ ታላቅ ስራ ለመስራት መዘጋጀቱን ያሳያል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

ግርማዊ

የንጉሥ ሀይል እና የንጉሥ አደራረግ

ራሱን አስታጠቀ

ቀበቶ መታጠቅ- አንድ ሰው ለስራ ወይም ለጦርነት ለመዘጋጀት በወገቡ ዙሪያ የሚታጠቀው ከቆዳ ወይም ሌላ ቁስ የተሰራ ማሰሪያ/መታጠቂያ

ዓለም በጽኑ ተመስርታለች

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "አንተ ዓለምን በጽኑ መሰረትክ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ሊንቀሳቀስ/ሊናወጥ አትችልም

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ማንም መቼም ሊያንሳቅሳት አይችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

አንተ ከዘለዓለም ድረስ ነህ

"አንተ ለዘለዓለም አለህ"