am_tn/psa/092/012.md

1.5 KiB

ጻድቅ እንደ ዘንባባ ዛፍ ያብባል

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች፤ ጻድቅ ሰዎች እንደ ጤናማ የዘንባባ ዛፍ ናቸው ምክንያቱም እነርሱ 1) ጠንካራ ይሆናሉ/ይበረታሉ ወይም 2) ሰዎች ያከብሯቸዋል፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የተተከሉ ናቸው

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ያህዌ ተክሏቸዋል" ወይም "ያህዌ እርሱ እንደ ተከላቸው ዛፎች ለእነርሱ እንክብካቤ ያደርጋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

በያህዌ ቤት…በአምላካችን በእግዚአብሔር አደባባዮች

ዘማሪው በእውነት እግዚአብሔርን ስለሚያመልኩ ሰዎች በያህዌ ቤት እንደሚያድጉ ዛፎች አድርጎ ይገልጻል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱ ያብባሉ

ዘማሪው ስለ ጻድቅ ሰዎች ጤናማ ዛፎች እንደሆኑ አድርጎ ይናገራል፡፡ "በጥሩ ሁኔታ ያድጋሉ" ወይም "በጣም ጠንካራ ናቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በአምላካችን አደባባይ

በእየሩሳሌም ቤተመቅደስ በሚገኘው አደባባይ