am_tn/psa/092/010.md

1.9 KiB

ቀንዴን እንደ ዱር በሬ/አውራሪስ ቀንድ ከፍ ከፍ አደረግህ

ዘማሪው እግዚአብሔር እንደ ዱር እንስሳ ጠንካራ እንዳደረገው ይናገራል፡፡ እዚህ ስፍራ የእርሱ "ቀንድ" የሚወክለው ጥንካሬውን ነው፡፡ "እንደ ዱር በሬ/አውራሪስ ጠንካራ አደረግኸኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

በለጋ ዘይት ተቀብቻለሁ

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች እግዚአብሔር በዘማሪው ላይ ያስቀመጠው ቅባት እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ለመሆኑ ዘይቤያዊ አነጋገር ነው 1) እርሱን ደስ ማሰኘቱ "አንተ እኔን በጣም ደስ አሰኘኸኝ" ወይም 2) እርሱን ጠንካራ አደረገው "አንተ እኔን ጠንካራ አደረግኸኝ" ወይም 3) ጠናቶችን እንዲያሸንፍ አስቻለው፣ "አንተ ጠላቶቼን እንዳሸንፍ አስቻልከኝ፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ዐይኖቼ የጠላቶቼን ውድቀት ተመለከቱ፤ ጆሮዎቼ የጠላቶቼን ክፉ ቀን ሰሙ

"ዐይኖች" እና "ጆሮዎች" የሚሉት ቃላት ለተመልካቹ እና ሰሚው ሰው ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ/ ነው፡፡ ስንኞቹ ሊጣመሩ ይችላሉ፡፡ "የክፉ ጠላቶቼን ሽንፈት አየሁ ደግሞም ሰማሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)