am_tn/psa/092/001.md

1.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ በዕብራውያን ስነግጥም ውስጥ የተለመደ ነው፡፡ (ስነ ግጥም እና ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

ለስምህ ውዳሴ/ምስጋና ማቅረብ

"የአንተ ስም" የሚሉት ቃላት "አንተ" ለሚለው ሜቶኖሚ /ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ "ለአንተ በውዳሴ መዘመር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በማለዳ የቃል ኪዳንህን ታማኝነት እናገራለሁ/አውጃለሁ

"ታማኝነት" የሚለው ረቂቅ ስም "ታማኝ" በሚለው ቅጽል ሊተረጎም ይችላል፡፡"አንተ ለቃል ኪዳንህ ታማኝ እንደሆንክ በማለዳ አውጃለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

በየምሽቱ የአንተን እውነተኝነት

ግሱ ከቀደመው ሀረግ ሊወሰድ ይችላል፡፡ "እውነተኝነት" የሚለው ረቂቅ ስም "እውነት" በሚለው ቅጽል ሊተረጎም ይችላል፡፡ "አንተ የምትናገረው ነገር ሁሉ እውነት መሆኑን በየምሽቱ እናገራለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የተተወ/የተዘለለ እና ረቂቅ ስሞች የሚሉትን ይመልከቱ)