am_tn/psa/091/005.md

2.4 KiB

በምሽት ሽብር

ዘማሪው ስለ "ሽብር" የሚናገረው በምሽት ጥቃት እንደሚያደርስ መንፈስ ወይም አስፈሪ እንስሳ እና እጅግ አስፈሪ ሰዎች አድርጎ ነው፡፡ "በምሽት ከሚያጠቁህ ነገሮች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በምሽት…በቀን

እነዚህ ሁለት ሀረጎች አንድ ላይ የተወሰዱት ማናቸውንም የምሽት ወይም የቀን ክፍለ ጊዜ ለማመልከት ነው፡፡ (ከጽንፍ ጽንፍ የሚለውን ይመልከቱ)

በቀን የሚበር/የሚፈናጠር ፍላጻ

እዚህ ስፍራ "ፍላጻ/ቀስት" ቀስት ለሚወረውሩ ሰዎች የዋለ ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ "በቀን በቀስት ጥቃት ከሚያደርሱብህ ሰዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ወይም ከሚከብህ መቅሰፍት

ዘማሪው ስለ ህመም የሚናገረው በሽታ ሰው ሆኖ ሰዎችን ለመግደል በምሽት እንደሚሄድ ሰው አድርጎ ነው፡፡ "በበሽታ የሚመጣ ሞት አያስፈራህም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

መንከራተት/መሄድ

በማናቸውም ጊዜ ወደሚፈልግበት ስፍራ ሁሉ መሄድ

በጨለማ…በቀትር ወቅት

እነዚህ ሁለት ሀረጎች በአንድነት ሆነው የሚያመለክቱት ሁሉንም የምሽት እና ቀን ጊዜያት ነው፡፡ (ከጽንፍ ጽንፍ የሚለውን ይመልከቱ)

በሽታ

በተመሳሳይ ጊዜ ብዙ ሰዎችን ህመም ላይ የሚጥል

በሺህ የሚቆጠሩ በጎንህ፣ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ በቀኝህ ሊወደወቁ ይችላሉ

"ብዙ ሰዎች በዙሪያህ ሊወድቁ ይችላሉ፡፡" ትክክለኛውን ቁጥር መተርጎሙ አንባቢዎችን ግራ የሚያጋባ ከሆነ፣ እነርሱን መተው ይቻላል፡፡

ይህ አይደርስብህም/አያገኝህም

"ክፉው አይጎዳህም"